facebookgoogle plustwitter

ሙሐመድ . . የመጨረሻውና የመደምደሚያው መልክተኛ

ሙሐመድ . . የመጨረሻውና የመደምደሚያው መልክተኛ

‹‹ምክንያቱም በዚያን ወቅት እግዚአብሔር እኔን ከምድር ላይ ይወስደኝና እኔን አሳልፎ የሸጠውን ከሓዲ መልኩን በመቀየር እኔን እንዲመስል ያደርገዋል፣ሰዎችም እኔ የተገደልኩ ይመስላቸዋል። እርሱ ይህን የውርደት ሞት ከሞተ በኋላም ክብሬን ተነፍጌ ለረዥም ዘመን በዓለም እኖራለሁ። ነገር ግን ቅዱሱ የእግዚአብሔር መልክተኛ ሙሐመድ በሚመጣ ጊዜ ይህ ውርደት ከኔ ይወገዳል።›› (በርናባስ ወንጌል ምዕ 112 ቁጥር 13-16)

ኦ አምላኬ!

ኦ አምላኬ!

‹‹የዘመናዊውን ስነፈለክ አንዳንድ ፎቶግራፎች ባየሁ ጊዜ የመጀመሪያ መስተጋብሬ ፦ ኦ አምላኬ! ሥራው ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል፤በሞቴ እጹብ ድንቅ ነገር ነው ብዬ መጮኽ ነበር።››

እስላም . . ሰላምና አማን ነው

እስላም . . ሰላምና አማን ነው

‹‹አይሁዶች በእስላም ሰንደቅ ስር ከጭቆና እና ከጥቃት ተጠብቀው ፍትሕን አግኝተዋል። ለበርካታ ምእተ ዓመታትም በመልካም አያያዝ የብልጽግና ኑሮ መርተዋል።››

እምነት . . እና ሕይወት

እምነት . . እና ሕይወት

‹‹እምነት የሰውን ኑሮ ለማገዝ የግድ መኖር ካለባቸው ኃይሎች አንደኛው ነው። እርሱን ማጣት ደግሞ የሕይወትን ጣጣዎች ለመጋፈጥ ድክመት መኖሩን ማስጠንቀቂያ ነው።››

በያንዳንዱ የሕይወት ዝርዝር ይገባል!!

በያንዳንዱ የሕይወት ዝርዝር ይገባል!!

‹‹እስላም ለሰው ልጆች ተመራጩ ሃይማኖት ነው። እስላም በያንዳንዲቱ የሙስሊም ሰው ሕይወት ዝርዝር ውስጥ ዘልቆ መግባት ብቻ ሳይሆን፣አንድ ሙስሊም በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የወሳኝነት ሚና አለው። በዛሬው ዓለም ላይ ከእስላም በስተቀር ሁሉንም የሰው ልጆች ችግር የመፍታት አቅም ያለው አንድም ሌላ ሃይማኖት አይገኝም። ይህ የእስላም ብቻ ሆነ ልዩ መለያው ነው።››

እንዴት ያለ ግፍ ነው?!

እንዴት ያለ ግፍ ነው?!

‹‹ሴት ከወንድ አኳያ እንደ ባሪያና እንደ ጌታ፣እንደ አእምሮ ሥራና የጉልበት ሥራ፣እንደ በርበርና እንደ ግሪካዊ ናት፤ሴት ልጅ ጎደሎ ሰው ስትሆን ከእድገት መስላል የታችኛው ደረጃ ላይ ቆማ እንድትቀር ተደርጋለች።››

ዒሳ . . እስላም ዘንድ

ዒሳ . . እስላም ዘንድ

‹‹እስላምን ባጠናሁ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ስሜት እውስጤ የፈጠረ የተለየ ሌላ የአልመሲሕ ዒሳን  ገጽታ ነበር ያየሁት።

ይለያል . .

ይለያል . .

‹‹እንደ እስላም ከዐረባዊው ነቢይ የቀደሙትን ነቢያትና መልክተኞች የሚያከብር ሌላ ሃይማኖት የለም። ነቢያቱን ማክበርና በነርሱ ማመንን በምእመናኑ ላይ ግዴታ አድርጎ ይደነግጋል። በመተላለፍና በመገለጥ ከርሱ የቀደሙትን መለኮታዊ ሃይማኖቶችንም እንደ እስላም የሚያከብር ሌላ ሃይማኖት አይገኝም።››

ተገቢው መሪ ዬት አለ?!

ተገቢው መሪ ዬት አለ?!

‹‹ስለ እስላም ተገቢውን ንግግር የሚናገር ተገቢው መሪ ከተገኘ፣ይህ ሃይማኖት ከመሰረታዊ ኃያላን ኃይሎች አንዱ ሆኖ በድጋሚ መውጣት ይችላል።››

ጠይቅ . . ቁርኣን መልስ ይሰጠሃል

ጠይቅ . . ቁርኣን መልስ ይሰጠሃል

‹‹ቁርኣን አጠናሁና ለሁሉም የሕይወት ጥያቄዎች መልሶችን አገኘሁበት።››