የነቢያትን ክብር ማዋረድ

የነቢያትን ክብር ማዋረድ

89
‹‹ኖኅም ገበሬ መሆን ጀመረ፣ወይንም ተከለ። ከወይን ጠጁም ጠጣና ሰከረ፤በድንኳኑም ውስጥ እራቁቱን ሆነ። የከነዓን አባት ካምም አባቱን ዕራቁትነት አየ፣ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌትም ሸማ ወስደው በጫንቃቸው ላይ አደረጉ፣ኋሊትም ሄደው አባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፣የአባታቸውንም እራቁትነት አላዩም። ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፣ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን፤ለወንድሞቹም ባሪያዎች ባሪያ ይሁን። እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባርክ፣ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን።›› ዘፍጥ. 9፣20-27 የባቢሎኑ ቴልሙድ ገጽ 70 ላይ ለዚህ ጥቅስ ማብራሪያ ሲሰጥ ከንዓን ወይም ካም ኖኅን ስልብ አድርገው ደፈሩት ይላል። ክቡሩ የአላህ ነቢይ ኑሕ  ግን ፈጽሞ ከዚህ የጠሩና የተጠበቁ ናቸው።

Tags:
Abdullah Awad Al Juhani - Quran Downloads