islamkingdomfaceBook islamkingdomtwitter islamkingdomyoutube islamkingdomnew


«»በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፡፡ ከጌታችሁ በተዓምር በእርግጥ መጣኋችሁ፡፡ የእስራኤልንም ልጆች ከእኔ ጋር ልቀቅ፡፡

(ፈርዖንም «በተዓምር የመጣህ እንደኾንክ ከውነተኞቹ ከኾንክ እርሷን አምጣት» አለው፡፡

በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ እባብ ኾነች፡፡

እጁንም አወጣ፡፡ እርሷም ወዲያውኑ ለተመልካቾች ነጭ ኾነች፡፡

ከፈርዖን ሰዎች መማክርቶቹ፡- «ይህ በእርግጥ ዐዋቂ ድግምተኛ ነው» አሉ፡፡

«ከምድራችሁ ሊያወጣችሁ ይሻል» (አሉ)፡፡ «ታዲያ ምን ታዛላችሁ» (አለ)

(እነርሱም) አሉ «እርሱንና ወንድሙን አቆይ፡፡ ወደ ከተሞቹም ሁሉ ሰብሳቢዎችን (ዘበኞች) ላክ፡፡»

«ዐዋቂ ድግምተኛ የኾነን ሁሉ ያመጡልሃልና፡፡»

ድግምተኞቹም ወደ ፈርዖን መጡ፡፡ «እኛ አሸናፊዎች ብንኾን ለእኛ በእርግጥ ዋጋ አለን» አሉ፡፡

«አዎን እናንተም በእርግጥ ከባለሟሎቹ ትኾናላችሁ» አላቸው፡፡

«ሙሳ ሆይ (በትርህን) ወይም (በፊት) ትጥላለህ ወይም እኛ ጣዮች እንኾናለን» አሉት፡፡

«ጣሉ» አላቸው፡፡ (ገመዶቻቸውን) በጣሉም ጊዜ የሰዎቹን ዓይኖች ደገሙባቸው፡፡ አስፈራሩዋቸውም፡፡ ትልቅ ድግምትንም አመጡ፡፡

ወደ ሙሳም፡- «በትርህን ጣል» ስንል ላክን፡፡ (ጣላትም) ወዲያውኑም የሚቀጣጥፉትን (ማታለያ) ትውጣለች፡፡

እውነቱም ተገለጸ፡፡ ይሠሩት የነበሩትም (ድግምት) ተበላሸ፡፡

እዚያ ዘንድ ተሸነፉም፡፡ ወራዶችም ኾነው ተመለሱ፡፡

ድግምተኞቹም ሰጋጆች ኾነው ወደቁ፡፡