islamkingdomfaceBook islamkingdomtwitter islamkingdomyoutube islamkingdomnew


አሉ፡- «በዓለማት ጌታ አመንን፡፡»

«በሙሳና በሃሩን ጌታ፡፡»

ፈርዖን አለ፡- «እኔ ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በእርሱ አመናችሁን ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰዎቿን ከእርሷ ለማውጣት በእርግጥ የተስማማችሁበት ተንኮል ነው፡፡ ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) ታውቃላችሁ፡፡»

«እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ፡፡ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ፡፡»

አሉ፡- «እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን፡፡»

«የጌታችንም ተዓምራቶች በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ ሙስሊሞች ኾነን ግደለን፡፡»

ከፈርዖንም ሰዎች ታላላቆቹ (ለፈርዖን) «ሙሳንና ሰዎቹን በምድር ላይ እንዲያበላሹና (ሙሳም) አንተንና አማልክቶችህን እንዲተው ትተዋቸዋለህን» አሉ፡፡ «ወንዶች ልጆቻቸውን እንገድላለን፡፡ ሴቶቻቸውንም እናስቀራለን፡፡ እኛም ከበላያቸው ነን፡፡ አሸናፊዎች (ነን)» አለ፡፡

ሙሳ ለሰዎቹ፡- «ለአላህ ተገዙ ታገሱም፡፡ ምድር ለአላህ ናትና፡፡ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፡፡ ምሰጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት» አላቸው፡፡

«ከመምጣትህም በፊት ከመጣኽልንም በኋላ ተሰቃየን» አሉት፡፡ «ጌታችሁ ጠላቶቻችሁን ሊያጠፋ እንዴት እንደምትሠሩም ይመለከት ዘንድ በምድር ላይ ሊተካችሁ ይሻል» አላቸው፡፡

የፈርዖንንም ቤተሰቦች እንዲገሰጹ በድርቅ ዓመታትና ከፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ ያዝናቸው፡፡