islamkingdomfaceBook islamkingdomtwitter islamkingdomyoutube islamkingdomnew


አላህም ከሰማይ ውሃን አወረደ፡፡ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው አደረገ፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡

ለናንተም በግመል፣ በከብት፣ በፍየል በእርግጥ መገምገሚያ አልላችሁ፡፡ በሆዶቹ ውስጥ ካለው ከፈረስና ከደም መካከል ጥሩ ወተትን ለጠጪዎች ተዋጭ ሲሆን እናጠጣችኋለን፡፡

ከዘምባባዎችና ከወይኖችም ፍሬዎች (እንመግባችኋለን)፡፡ ከእርሱ ጠጅንና መልካም ምግብንም ትሠራላችሁ፡፡ በዚህም ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡

ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አስታወቀ «ከተራራዎች፣ ከዛፍም፣ (ሰዎች) ከሚሠሩትም (ቀፎ) ቤቶችን ያዢ፡፡

«ከዚያም ከፍሬዎች ሁሉ ብይ፡፡ የጌታሽንም መንገዶች (ላንቺ) የተገሩ ሲኾኑ ግቢ፡፡» ከሆዶችዋ መልኮቹ የተለያዩ መጠጥ ይወጣል፡፡ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መድኃኒት አለበት፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለበት፡፡

አላህም ፈጠራችሁ፤ ከዚያም ይገድላችኋል፡፡ ከእናንተም ከዕወቅት በኋላ ምንንም ነገር እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፡፡ አላህ ዐዋቂ ቻይ ነው፡፡

አላህም ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በሲሳይ አበለጠ፡፡ እነዚያም በላጭ የተደረጉት ሲሳያቸውን እጆቻቸው በያዙዋቸው (ባሮች) ላይ እነሱ በእርሱ ይተካከሉ ዘንድ መላሾች አይደሉም፡፡ ታዲያ በአላህ ጸጋ (ለእርሱ ተጋሪ በማድረግ) ይክዳሉን

አላህም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ለእናንተ ሚስቶችን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከሚስቶቻችሁ ወንዶች ልጆችን፣ የልጅ ልጆችንም አደረገላችሁ፡፡ ከመልካሞችም ጸጋዎች ሰጣችሁ፡፡ ታድያ በውሸት (በጣኦት) ያምናሉን በአላህም ጸጋ እነሱ ይክዳሉን