islamkingdomfaceBook islamkingdomtwitter islamkingdomyoutube islamkingdomnew


(አላህ) አለው «እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡

ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡»

በላቸው «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም፡፡

«እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

«ትንቢቱንም (እውነት መኾኑን) ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡»

የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊው ጥበበኛው ከኾነው አላህ ነው፡፡

እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት (የተመላ) ሲኾን አወረድነው፡፡ አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡

ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም፡፡

አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው፡፡

ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፡፡ ንቁ! እርሱ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡