islamkingdomfaceBook islamkingdomtwitter islamkingdomyoutube islamkingdomnew


እርሱም ሁለቱን ዓይነቶች ወንድንና ሴትን ፈጠረ፡፡

ከፍትወት ጠብታ (በማህጸን ውስጥ) በምትፈሰስ ጊዜ፡፡

የኋለኛይቱም ማስነሳት በእርሱ ላይ ነው፡፡

እነሆ እርሱም አከበረ፣ ጥሪተኛም አደረገ፡፡

እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡

እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል፡፡

ሰሙድንም (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም፡፡

በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፡፡ እነርሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነርሱ ነበሩና፡፡

የተገለበጠችውንም ከተማ ደፋ፡፡

ያለበሳትንም አለበሳት፡፡

ከጌታህም ጸጋዎች በየትኛው ትጠራጠራለህ?

ይህ ከፊተኞቹ አስፈራሪዎች (ጎሳ) የኾነ አስፈራሪ ነው፡፡

ቀራቢይቱ (ኅልፈተ ዓለም) ቀረበች፡፡

ለእርሷ ከአላህ ሌላ ገላጭ የላትም፡፡

ከዚህ ንግግር ትደነቃላችሁን?

ትስቃላችሁምን? አታለቅሱምን?

እናንተም ዘንጊዎች ናችሁ፡፡

ለአላህም ስገዱ ተገዙትም፡፡

ሰዓቲቱ (የትንሣኤ ቀን) ተቃረበች፤ ጨረቃም ተገመሰ፡፡

ተዓምርንም ቢያዩ (ከእምነት) ይዞራሉ፡፡ (ይህ) «ዘውታሪ ድግምት ነውም» ይላሉ፡፡

አስተባበሉም፡፡ ዝንባሌዎቻቸውንም ተከተሉ፡፡ ነገርም ሁሉ (ወሰን አለው)፤ ረጊ ነው፡፡

ከዜናዎችም በእርሱ ውስጥ መገሰጥ ያለበት ነገር በእርግጥ መጣላቸው፡፡

ሙሉ የኾነች ጥበብ (መጣቻቸው) ግን አስፈራሪዎቹ አያብቃቁም፡፡

ከነርሱም ዙር፡፡ ጠሪው (መልአክ) ወደ አስደንጋጭ ነገር የሚጠራበትን ቀን (አስታውስ)፡፡